Folk psychology

Folk psychology የሚሰኘው የጥናት ዘርፍ በዋነኝነት ትኩረት አድርጎ የሚያጠናው በእያንዳንዱ ማህበረሰቡ ውስጥ በታሪክ በባህል እና ተያያዥ እሴቶች የሚፈጠሩ እውቀቶች እና ፍልስፍናዎችን ነውⵆ። በዚህ የጥናት ዘርፍ ላይ ጥልቅ ምርምር ያደረጉ ሙያተኞች እንደሚናገሩት አንድ ማህበረሰብ በታሪክ ሂደት የሚያጎለብታቸውን ማህበረሰባዊ እውቀቶች በተረት በአባባል እና በምሳሌዎች ከትውልድ ወደ ትውልድ ያሻግራቸዋል።ⵆ እነኚህ እውቀቶች ለእያንዳንዱ ግለሰብ ስነልቦናዊ እድገት እና ጤንነት ከፍተኛ ድርሻ አላቸው! የእያንዳንዱን ማህበረሰብ ማህበረሰባዊ ድር ከማስፋት እና ከማጠንከር አንፃርም እነኚህ እውቀቶች ጉልህ ድርሻ አላቸው። ተግባራዊ ለሆኑት እንደ ህክምና ስነከዋክብት አስተዳዳራዊ ፍልስፍናዎች እና የቁጥር ትምህርት እድገትም ይህ እውቀት የራሱ ጉልህ ድርሻ አለውⵆ።

በዚህ በማህበረሰብ የታሪክ ቅብብሎሽ የሚያድገው እውቀት ጎልቶ ከሚታይባቸው አገራት በቀዳሚነት ተርታ የምትሰለፈው አገራችን ኢትዮጵያ ናት። አገራችን የሰባት ሺህ ዘመናት የታሪክ ባለፀጋ እንደመሆኗ ጥንታውያን አያቶቻችን በተረቶቻቸው በምሳሌያዊ ንግግሮቻቸው በስነ ቃሎቻቸው እና በምክሮቻቸው የነበሯቸውን ከዘመኑ ሳይንስ የነጠሩ እውቀቶችን አውርሰውናል። 
እነኚህ እውቀቶች በተለያዩ ዘመናት በአገራችን ተነስተው ለነበሩ ስልጣኔዎች የራሳቸው ጉልህ ድርሻ ነበራቸው። ለምን ቢሉ እነኚህ እውቀቶች የመሪዎችንም ሆነ የተመሪዎችን Emotional and spiritual Intelligence የማበልፀግ አቅም ስለነበራቸው ነው! የስነልቦና ሳይንስ እንደሚጠቁመው መሪ እና ተመሪን በአንድነት ሰርተው አስደናቂ ብሎም ለትውልድ የሚተርፍ ስራ እንዲከውኑ ራሳቸውን ማበልፀግ ወይም ማብቃት ይኖርባቸዋል! ይህ ብቃት ደግሞ self-actualization ይሰኛል። ይህ ራስን ማብቃት ወይንም ደግሞ self-actualization የሚመጣው እያንዳንዱ ግለሰብ ራሱን በሶስት የእውቀት ብሎም የሕይወት ዘርፎች ማበልፀግ ሲችል ነው። እነርሱም ከላይ እንደተመለከትነው IQ EO እና SQ የሚሰኙት ናቸውⵆ። ከነርሱም መካከል EO እና SQ በ Folk psychology በሚጠኑት ማህበረሰባዊ እውቀቶች የሚበለፅጉ ናቸው! ይህን ያህል ነው ማህበረሰባችን ለዘመናት ያካበታቸው እውቀቶች የሚበጁንⵆ ግለሰብን ቤተሰብን ማህበረሰብን መሪዎችን እና አገራትን በብዙ መልኩ የማብቃት እና የማጎልበት ሀይል አላቸውⵆ።

የኛ ትውልድ ግን እነኚህ ከማህበረሰባችን በተረቶች እና በስነቃሎች የወረሳቸውን እውቀቶች ፍልስፍናዎች እና ልምዶች ሲንቃቸው እና ሲዘባበትባቸው እያስተዋልን እንገኛለንⵆ። ካልተማረው አንድ ግለሰብ አንስቶ ምሁራን ነን እስከሚሉ አንዳንድ ሰዎች ጨምሮ እነኚህን የማህበረሰባችን እውቀቶች ሲንቁ ማስተዋል የተለመደ ሆኗልⵆ። እነኚህን እውቀቶች አጥንቶ ለተግባራዊ ሳይንሳዊ እውቀቶች እንዲተገበሩ ማድረግ የሚጠበቅባቸው የትምህርት ተቋማትም ሆኑ መንግስታዊ ተቋማትም ችሏ ያሉት የእውቀት ዘርፍ ነው። የኪነጥበብ ባለሙያ ነን ብለው ፊልም እና መፅሐፍ የሚያመርቱ ሙያተኞችም ቢሆን እነዚህ ማህበረሰባዊ ፍልስፍናዎች እና እውቀቶች ላይ ሲዘባበቱ ማየት የተለመደ ሆኗልⵆ ግን ለምን ይሆን ? 
ምእራቡ አለም እኮ ባህር ተሻግረው እነሱን እንድንመስል የነርሱን ቅርፅ እንድንይዝ ካስቻሉበት መሳሪያቸው አንዱ ይህ የነርሱ ማህበረሰብ ያጎለበተው ፍልስፍና ነውⵆ ። ባለቻቸው የመቶ ዘመናት ታሪክ ያገኙትን ይህን ማህበረሰባዊ እውቀት በታሪክ መፅሐፎቻቸው በፊልሞቻቸው በሳይንሳዊ እውቀቶቻቸው እና በፖለቲካዊ ፅንሰ ሀሳቦቻቸው ላይ በመተግበር ማጎልበት ችለዋል።ⵆ አለምን እነርሱ በፈለጉት መልኩ ለመቅረፅም እንደ መሳሪያ ተጠቅመውባቸዋልⵆ።
እና እባካችሁ ከቤተሰቦቻችሁ ከጎረቤቶቻችሁ በተረት ሆነ በስነቃሎች ብሎም በምሳሌዎች ያገኛችሁትን እውቀቶች በሚገባ አጎልብቷቸው! ምክሮቻቸውንም በህይወታችሁ በመተግበር ራሳችሁን አበልፅጉባቸውⵆ! እናንተ ያወቃችሁትንም ሌሎች እንዲያውቁት ንገሩ አስተምሩ አካፍሉ! በተለይ በተለይ ማህበራዊ ድረገፆችን ይህን የማህበረሰባችን እውቀት ለማካፈል ለማስተዋወቅ እና ለማጎልበት እንጠቀምበት! ስልኮቻችሁ ኮምፒውተሮቻችሁ ብሎም ታቦቻችሁ ላይ እነኚህን ማህበረሰባዊ እውቀቶች ለመመዝገብም ተጠቀሙባቸው! በተረፈ በዚህ አጭር መልእክቴ ላይ ባጎደልኩት እናንተ ሙሉበት!

ጥንታዊነት የዘመኑ ፋሽን ነው!
ራፋቶኤል

 

 

 

ይከተሉን!