የምስጢራዊው መፅሐፍ እንቆቅልሽ ተፈታ

አለምአቀፍ መገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት የምስጢራዊው መፅሐፍ እንቆቅልሽ ተፈታ ምስጢሩም ተገለጠ ኢትዮጵያም ዋጋ ተሰጣት [ credit] ።

አለምአቀፍ ምሁራን Voynich በመባል በሚታወቀው መፅሐፍ ላይ የሚገኙትን ምስጢራዊ ፅሁፎች ስእሎች እና ምልክቶች ለመረዳት ዘመናትን ፈጅቶባቸዋል። ይህ Voynich manuscript እየተባለ የሚጠራው ጥንታዊና ምስጢራዊ መፅሐፍ Wilfred Voynich በተባለ ሰው ስም ነው የተሰየመው። ይህ ሰው መፅሐፉ የአለም ምሁራንን ትኩረት እንዲያገኝ የረዳ ነው። ለዚህም ውለታ ነው በእርሱ ስም መፅሐፉን የሰየሙት። ይህ መፅሐፍ በአሁን ወቅት Library of yale university ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ይህን ተቋም ጨምሮ በተለያዩ የአለም ክፍል ያሉ ምሁራን [ Code breaking experts] ተሰባስበው ረጅም ዘመናትን የፈጀ ጥናት ቢያደርጉም የመፅሐፉ ይዘትና ምስጢር ሊፈታ ባለመቻሉ ነው። ለዚህም ዋንኛው መንስኤ ለሰው ልጅ እንግዳ በሆነ ቋንቋ መፃፉ ነው። አንዳንዶች የአፃፃፍ ዘይቤውን "alien characters " ብለው ስያሜ ለጥፈውለታል። በስተመጨረሻ ግን አንድ መልካም ዜና ተሰማ። Viekko Latvala የተሰኘ የፊንላንድ ዜግነት ያለው ሰው የዚህን መፅሐፍ እንቆቅልሽ ፈትቻለሁ በማለት ምስጢሩን ለአለም ይፋ አደረገ። እንደዚህ የጥናት ሰው ገለፃ መሰረት መፅሐፉ ስድስት ክፍሎች አሉት። የእፅዋት ህክምና፣ የስነህዋ እውቀት፣ ስለከዋክብት፣ የስነህይወት እውቀት፣ የመድሀኒት አቀማመም እና የመድሃኒት ገቢር [ recipes] ላይ ትኩረት ያደረጉ ናቸው። ባለሙያው ከዚህ ጋር አያይዞ ይፋ ያደረገውን መረጃ አለምአቀፍ መገናኛ ብዙሃን በተለይም fox news የዘገበው ሲሆን በዚህ አስደናቂ መፅሐፍ ውስጥ የመድሃኒት አቀማመም እና የእፅዋት ህክምናን ክፍል ላይ ለመድሃኒትነት የሚያገለግሉት እፅዋት #ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚገኙ መፅሐፉ ያትታል። 

ይህ መረጃ ስላነቃኝ ከድረገፆች ላይ ስለመፅሐፍ የበለጠ መረጃ ለማግኘት ስበረብር ያገኘኃቸውን የመፅሐፉ ገፅ የያዙ ፎቶዎችን ተመለከትኩ። አብዛኛዎቹ አሳሳላቸውና ቅርፃቸው ከኛው ጥንታዊ መፅሐፍ #እፀ_ደብዳቤ ላይ ከሚገኙት ጠልሰሞች ጋር ተዛምዶ አግኝቸዋለሁ። ስእሎቹ ብቻ ሳይሆን የመፅሐፎቹ ይዘትም ይዛመዳል። ምክንያቱም እንደሚታወቀው እፀ ደብዳቤ የተሰኘው መፅሐፋችን ትኩረቱ ለመድሃኒትነት ስለሚያገለግሉ እፅዋት፣ ስለ አቀማመማቸው እና ስለገቢሩ ማለትም ስለ recipes ነው። ፀሐፊውና የተፃፈበት ቋንቋ ያልታወቀው voynich manuscript ለመድሃኒትነት የሚያገለግሉት እፅዋት መገኛ ኢትዮጵያ ነች ብሎ ፍንጭ መስጠቱ ማን እንደፃፈው የማወቅ ጉጉቴን ከፍተኛ አድርጎታል። ማንም ቢፅፈውም የፃፈው አካል ስለጥንታዊ የኢትዮጵያውያን እውቀት እና ስለአገሪቱ መልክአምድር የጠለቀ እውቀት እንዳለው መረዳት ይቻላል። ምክንያቱም በኢትዮጵያ ይገኛሉ ተብሎ የተጠቀሱት እፅዋት የኢትዮጵያውያን የዘርፉ ሊቃውንት እንኳ በቀላሉ የማያገኟቸው ናቸው። ስለ እፅዋቱ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት እውቀታቸው እንደሊቃውንቱ ይለያያል። ጥንታዊነታችን እና ጥንታዊ እውቀቶቻችን ይህን ያህል የተቀረው አለም ላይ ተፅእኖ ፈጥረዋል። ለዚህ ነው #ጥንታዊነት_የዘመኑ_ፋሽን_ነው የምንለው።

ምንጭ: fox news 

#ራፋቶኤል

 

 

 

ይከተሉን!