የጥቁር የበላይነት

melanin #የጥቁርየበላይነት #ኢትዮጵያ #አንድነት #የነጮችየበታችነት_ስሜት_እና_ቅናት #ጥቁርውበት

እኛ ኢትዮጵያን እና መላው ጥቁር ወንድሞቻችን እኮ ከተቀረው አለም ታሪካችን የተለየ ነው፣ እምነታችን የተለየ ነው ፣ ባህላችን የተለየ ነው፣ ስልጣኔያችን የተለየ ነው፣ እሴቶቻችን የተለዩ ናቸው፣ አበላላችን የተለየ ነው፣ ፍልስፍናችን የተለየ ነው ፣ ስነልቦናችን የተለየ ነው። መለየት ብቻ አይደለም ጥንታዊና ከነጮቹ የመቶ አመታት ታሪክ በሺህ አመታት ይልቃል። እነሱ ያላቸው እኛ አለን እኛ ያለን እነሱ የሌላቸው ሊኖራቸውም የማይችሏቸው እጅግ በርካታ ነገሮች አሉ። እነዚህም ተፈጥሯዊ የሆኑ ግብአቶችንም ያካተተ ነው። ለምሳሌ እኛ ኢትዮጵያውያን በፈጠራ በአስተሳሰብ እና በፍልስፍና ብሎም በውጫዊ አካላዊ ውበት እንድንልቅ ካስቻሉን ተፈጥሯዊ ግብአቶች አንዱ Melanin ነው። ሜላኒን በአእምሯችን እና በሰውነታችን ህብለ በራሂ ውስጥ የሚገኝና ለእውቀት እና ለፈጠራ ምንጭ የሆነ ህዋስ ነው። ይህ የሰውን ልጅ ፈጠራ እና እውቀት የሚያበለፅገው ህዋስ በጥቁሮች ማለትም በኛ በአፍሪካውያን ውስጥ ብቻ የሚገኝ ነው። ይህም በነጮቹ የስነ ህዋ ሊቃውንትም የተረጋገጠ ነው። ገብቶሀል ላለፉት ሰባት ሺህ ዘመናት ድንቅ ታሪክና ስልጣኔ አፍሪካ መገንባት የቻለችው በዚህ በኛ ደም ውስጥ ብቻ በሚገኘው የሜላኒን ተፈጥሯዊ ህዋስም ነው። እንደሚታወቀው አገራችን ኢትዮጵያ የአፍሪካ እና የአፍሪካውያን ወላጅ እናት ናት። ከዚህ በተጨማሪም የምአራቡ አለም የስነህይወት ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከሆነ በሰው ልጆች ውስጥ የሚገኙት እያንዳንዶቹ ጥቃቅን ህዋሶች 23 ጥንድ ህብለበራሂ(Chromosome) ይይዛሉ፡፡ በአጠቃላይ 46 ህብለበራሂ(Chromosome) የሚገኙ ሲሆን ሀያሁለቱ “autosomes” የሚባሉ ሲሆኔ አንዷ የቀረችው ጥንድ የሰውን ልጅ ፆታ የምትለይ ናት፡፡እንዲሁ በእያንዳንዱ ህዋስ ውስጥ “ Mitochondria” ይገኛል፡፡ Mitochondria የህዋስ የሀይል ቤት እየተባለ የሚጠራ ሲሆን “oxidative phosphorylation” በተሰኘ ሂደት አማካይነት ለሰውነታችን ሀይልን ያመነጫል፡፡ በተጨማሪም በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙት ህዋሶች ራሳቸውን የማጥፋት ሂደታቸውን(Apoptosis) እንዲቀንሱ የመቆጣጠር ስራን ያከናውናል፡፡ ታዲያ ይህ የህዋሳት የሀይል ቤት (Mitochondria) የሰው ልጅ የሚያገኘው ከእናቱ ብቻ ነው፡፡ ይህን ተፈጥሯዊ ሂደት መሰረት በማድረግ በ1987(እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር) Rebecca cann, Mark Stoneking እና Allan Wilson የተባሉ የስነህይወት ምሁራን አንድ ጥናት አደረጉ፡፡ ባደረጉት ጥናት መሰረት ሁሉም የሰው ዘር በህዋሱ ውስጥ የሚያገኘው የህዋሳት የሀይል ቤት (Mitochondria DNA) መነሻ እጅግ ከበርካታ ሺህ ዘመናት በፊት በምስራቅ አፍሪካ(ኢትዮጵያ) ውስጥ ትኖር የነበረችና የሰው ዘር መነሻ የሆነች ከመጀመርያ ሴት ፍጥረት እንደሆነ አረጋግጠዋል። ይህን የጥናት ውጤታቸውን ሲያሳትሙም ከዚች ከመጀመርያ ሴት የተገኘውን የህዋስ ክፍል Mitochondrial Eve(ሄዋን) ብለው የሰየሙት ሲሆን ሌሎች ምሁራን ደግሞ አፍሪካዊ ሄዋን( African Eve) ብለው ጠርተውታል፡፡ አሁን በአለም የሚገኙ የሰው ዘሮች እያንዳንዳቸው በተፈጥሮ ያገኙት የህዋሳት የሀይል ቤት (Mitochondria) እንግዲህ መነሻው በምስራቅ አፍሪካ ኢትዮጵያ ውስጥ ትገኝ ከነበረችው የመጀመርያዋ ሴት ሄዋን ነው ሲሉ የምእራቡ አለም ምሁራን የተለያዩ ንድፈ ሀሳቦችን እያቀረቡ ይገኛሉ ፡፡ ለዚህ ንድፈ ሀሳባቸውም የይዘተ በራሂና የስነምድር ጥናታቸውን በማስረጃ አስደግፈው በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡

ይህ የምእራቡ አለም (Mitochondria Eve) ንድፈ ሀሳብ ኢትዮጵያ አገራችን የሰው ዘር መነሻ መሆኗን ብቻ ሳይሆን አዳምና ሄዋንም በኢትዮጵያ ምድር ውስጥ ይገኙ እንደነበር እሌያም ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ለሚደረጉ ጥናቶች በር ከፋች ነው፡፡ ምን መሰለህ እየነገርኩህ ያለሁት አገራችን የሁሉ ነገር መሰረት ናት! ተፈጥሮም ለኛ አድልታ ብዙ ስጦታ ሰጥታናለች። በዚህም ነጮቹ የበታችነት ስሜት ይሰማቸው ነበር። ለዛም ነው ላለፉት አመታት ጥቁሮችን እና ተፈጥሯዊ አቅማችንን አድቅቀው አጥፍተው የበላይ ለመሆን አንገታቸውን ደፍተው ሲያሴሩ የኖሩት። ማሴር ብቻ አይደለም ስኬታማ የሆነ እስትራቴጂ ይዘው በመምጣትም እኛን ከእግራቸው በታች አድርገው እነሱ የበላይ መሆን ችለዋል። እንዴት አትለኝም? 

ይኸውልህ ከውጭ የሚገቡ አብዛኛዎች የታሸጉ ምግብ እና መጠጦች፣ ሳሙናዎች እና የውበት መጠበቂያ ግብአቶች በቀጥታ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘውን MELANIN በሚያዳክሙ ንጥረነገሮች የተፈበረኩ ናቸው። በብዙ ቢሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት በአፍሪካ ላይ የዘረጉት የፖለቲካ፣ የትምህርት እና የመዝናኛ እና የመገናኛ ስርአታቸው የኛን የአፍሪካውያንን የአእምሮ አቅም የሚያዳክም ነው። በአፍሪካ ታሪክ ውስጥ የተፈጠሩ የርስ በርስ ግጭቶች እና ጭፍን የዘረኝነት አጥፍቶ መጥፋት ሴራዎች የተቀነባበሩት እና ሲመሩ የነበሩት በነጮቹ ነው። ነጮቹ በኛ ይቀናሉ! ነጮቹ በኛ የበታችነት ስሜት ይሰማቸዋል። ለዛ ነው ላለፉት መቶ አመታት የጥቁር ህዝብን በዘር በጎሳ በጎጥ በእምነት በኢኮኖሚ ከፋፍለው አበጣብጠው አጨራርሰውን ሊያጠፉን ሲሰሩ የነበሩት። ወዳጄ ዘረኝነት እና ጠባብ ብሔርተኝነት እኛን ለመጣል የተዘረጋ መረብ ነው። አንድ ስንሆን ሀይላችንን ያውቁታል። አድዋ ላይ ቀምሰውታላ። ለዛ ነው አንድነትህን የሚነጥቅ የቤት ስራ የሰጡህ። ከነዛም መካከል አንዱ ዘረኝነት እና ጠባብ ብሔርተኝነት ዋንኛው ነው። ይሄ ዘመን አንድ በመሆን የነጮችን የበላይነትን በመቆጣጠር ኢትዮጵያን ብሎም አፍሪካን የበላይ ለማድረግ የምንታገልበት እንጂ በነሱ መረብ ውስጥ ተጠምደን እርስ በእርስ የምንጫረስበት አይደለም። ኧረ በማርያም ንቁ! ትልቁን ስዕል ለመመልከት እንሞክር! ውጊያው አይደለም ተነጣጥለን አንድ ሆነንም ከባድ ነው። ነገር ግን እኛ አሸናፊ ሊያደርጉን የሚችሉ የታሪክ እና ተፈጥሯዊ ስጦታዎች አሉን። እነሱ ላይ ትኩረት እናድርግ! ለማሸነፍ ከሚለዩን ይልቅ አንድ የሚያደርጉን እሴቶች ላይ ትኩረት እናድርግ። ለመለያየት ሳይሆን አንድ ሆነን ለመስራት እንትጋ።

#ራፋቶኤል

 

 

 

ይከተሉን!