ጎጃም እና ያልተነገረው ታሪኳ2

25 ሜትር ርዝመት የነበረው ኢትዮጵያዊው ግለሰብ ባናይ መካነ መቃብር በጎጃም ተገኘ!

ባናይ የሚባለው ግለሰብ መካነ መቃብር የተገኘው በአማራ ብሄራዊ ክልል በምዕራብ ጎጃም ዞን ወምበርማ ወረዳ በጎመር ዶንድ ቀበሌ በደኪ ንዑስ ቀበሌ ውስጥ ነው፡፡ 25 ሜትር ርዝመት ያለው መካነ መቃብር በጎመር ዶንድ እና ኮሊ ቀበሌ ድንበር ከምስራቅ ወደ ምዕራብ በ25ሜትር ርዝመት ላይ አርፏል የባናይ መቃብር፡፡ በወቅቱ ይህን ያህል ርዝመት ያለው ሰው ይኖር ይሆን የሚለውን ጉዳይ እውንነት ለማጣራት ስለግለሰቡ ማንነትና መካነ መቃብሩ የተሻለ እውቀት ና መረጃ ያላቸው የዕድሜ ባለፀጋዎች ስለ ሁኔታው ያስረዳሉ፡፡ የኮሊ ቀበሌ ናዋሪ የሆኑ አዛውንት አባ ደጀኔ ባሻ ከአያቶቻቸው ና ከዘመዶቻቸው የሰሙትን በዘመኑ ስለነበረው ሰው ምንም የጹሁፍ መረጃ ባያገኙም የመቃብሩን አቀማምጥ ስለ ዘር ግንዱ ስለ አካሉ ግዙፍነት ስለ ባህሪው ሁለተናዊ ስብዕናው ይናገራሉ፡፡ ባናይ በጣም ግዙፍና አስደናቂ ስው እንዲሁም የተለየ ፍጡር እነደሆነ ያስረዳሉ፡፡ በተጨማሪ የባናይ የስጋ ዝምድና ያላቸው በዕድሜ የገፉ አዘውንት አባ ብሩ አወቀ የባናይ የትውልድ ስፍራ በአማራ ክልል በመዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ወረዳ አዳል መዳሀኒአለም ቀበሌ እደሆነና አባቱም ጉራቻ እንደሚባልና እናቱ ደግሞ ገሞና እንደምትባል ከዘመዶቻቸው የሰሙ እንደነበረ ይናገራሉ፡፡ ባናይ በጣም የተለየ ፍጡር እነደሆነና አስገራሚ ታሪክ ያለው ሰው እንደሆነ አባ ብሩ ከአያት ከቅደመአያቶቻቸው የሰሙትን ያወሳሉ፡፡ 

ባናይ ቁመቱ ከ25ሜትር በላይ እነደሆነና አመጋግቡም የተለየ እንደሆነ ሲናገሩ በአንድ ጊዜ ለራት ወይም ለምሳ ከሰባት ቂጣ በላይ እነደሚበላ ና አንድ አነስተኛ እንስራ ሙሉ (አንድ ገምቦ ጠላ) እነደሚጠጣ ይናገራሉ፡፡

ባናይ ቁመቱ እጅግ ከመርዘሙ የተነሳ ቁጭ እንዳለ ከአንድ ዛፍ ጫፍ ቅጠል ቆርጦ እነደሚፀዳዳ አጨውተውናል፡፡

ባናይ ከድምበረ ይገባኛል ጥያቂ ባሻገር የሚመራቸውን ጎሳዎች የተለያየ ነገር ገብሩለኝ እያለ ሲያስቸግር እንደቆየና በመጨረሻም የሽመል ሙቀጫ ገብሩልኝ እያለ የአካበቢውን ህብረተሰብ እጅግ በማስቸገሩ ህብረተሰቡን በጉልበት(በጦርነት) ስላልቻሉት መላ መፈለግ ጀመሩ፡፡ ይህውም ለባናይ የምትሆነው ሚስት እንዳጣ ያስተዋለው የአገሪው ቤተሰብ ከጌርጆ ጎሳ የሆነች ሴት እንዳጩለት ይነገራል፡፡ ስለዚህ አስደናቂ ግለሰብ መካነ መቃብሩ ብቻ አይደለም መረጃ ሆኖ የተገኘው! በዘመኑ በአንድ አጋጣሚ በብስጭት የወረወረው ድንጋይም ጭምር እንጂ! ነገሩ እንዲህ ነው : 

ከወረዳው ርዕሰ ከተማ ከሽንዲ በወገዳድ እስከ ጎመር ዶንድ ቀበሌ 24 ኪ.ሜ የጠጠር መንገድ በትራንስፖርት ከዚያም እስከ ደኪ ንዑስ ቀበሌ ከ6-7 ኪ.ሜ ርቀት በእግር በመጓዝ የፋንግራይ ቀጤ ትክል ድንጋይ የሚገኝበት ቦታ ይደርሳሉ፡፡ የፋንግራይ ቀጤ ትክል ድንጋይ ቁመቱ 8ሜትር ዙሪያው 25ሜትር ሲሆን በወቅቱ በነበረው የድንበር ግጭት ፋንግራይ የተባለው የጎሳ መሪ ለጎመር ዶንድ ቀበሌና ለቀንጠፍን ቀበሌ ድንበር እንዲሆን ይህንን ድንጋይ በእጁ ወርውሮ እንዳቆመው በአካባቢው የዕድሜ ባለፀጋ አባ አላምረው ቀኖ እና አባ ደጀኔ ባሻ ይናገራሉ፡፡ ፋንግራይ ይህን ቀጤ ድንጋይ የወረወረውና የተከለው የራሱ ጎሳ ይዞታ የነበረውን የጎመር ዶንድ ቀበሌ ይዞታ ለማስፋፋት እንደሆነ ከአባቶቻቸው የሰሙትን ይናገራሉ፡፡ በመሆኑም ፋንግራይ ድንጋዩን ከጎመር ዶንድ ይዞታ አንስቶ ወደ ቀንጠፍን (ሰማሆን) ይዞታ ወርውሮ እንዳቆመውና ድንጋዩም በዚህ ጎሳ የመሪ ስም እንደተሰየመ ይናገራሉ፡፡ ስለ ፋንግራይ አካላዊ እና መንፈሳዊ ሁኔታ በግልጽ ባይታወቅም ፋንግራይ የባናይ ወንድም ስለመሆኑና የተለየ ተፈጥሮዊ ጥንካሬና ስጦታ የነበረው ሰው እንደነበር ታሪክ አዋቂዎችና የእድሜ ባለፀጋ የሆኑት ይናገራሉ፡፡

በዚህ አስደናቂ ታሪክ በእጅጉ ተደስቻለሁ! ምክንያቱም ከጎጃም ጥንታዊ የስልጣኔ ስፍራነት አንፃር ብዙ የተበታተኑ ነገር ግን አስደናቂ መረጃዎችን ባገኝም በመረጃ እጥረት ይዤ የቆየኃቸው አንዳንድ እውነታዎች አሉ! መረጃ ባለመግኘቴ ተስፋ ቆርጬ የተወኳቸው ጥናት ርዕሶችም ነበሩኝ! ዛሬ ግን ደስ ብሎኛል! ለምን? ይሄ የባናይ እና የርሱ የዘር ሀረግ ጋር ተያይዞ ያገኘሁት ይሄ መረጃ ጥናቴን ለመቀጠል በእጅጉ አነሳስቶኛል! ራሱን ችሎ ሌላ አንድ የታሪክ ምንጭም ነው! ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ይኑር በእውነት! 

ከስር ያያያዝኩት ምስል ከታሪኩ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው ሲሆን በሌላ አገር የተገኘ ነው! ሀሳቡን ለመግለፅ ብቻ የተጠቀምኩበት ነው! በዚሁ አጋጣሚ መረጃውን ላጠናቀረው እና በማህበራዊ ድረገፁ ላካፈለን የወምበራ ባህልና ቱሪዝም አድናቆቴን እና ምስጋናዬን ለመግለፅ ወዳለሁ! ራፋቶኤል ! 

ምንጭ፡- የወምበርማ ወረዳ ባቱ ጽ/ቤት 

በሽንዲ መሪ ማ/ቤት እና በወም/ወ/ኮሙ/የመ/ኢን/ስ/ሂ

 

 

 

ይከተሉን!